#short | Ethiopia: ሰበር| ዓለም አቀፍ የአደገኛ እፅ አዘዋዋሪዎች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ። | Zehabesha

3 years ago
3

#short
ዓለም አቀፍ የአደገኛ እፅ አዘዋዋሪዎች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

መነሻቸውን ብራዚል ሳኦፖሎ መዳረሻቸውን ደግሞ ዱባይና ናይጄሪያ በማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩ የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ሁለት ናይጄሪያዊያንና አንዲት ብራዚላዊት ሲሆኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገባቸው ፍተሻ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ አደገኛ ዕፁን በውስጣዊ የሻንጣ አካል በመደበቅና ውጠው በሆዳቸው በመያዝ ለማሳለፍ ሙከራ ቢያደርጉም የፌደራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት የተጠናከረ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢንስፔክተር አዲሱ ባለሚ ገልጸዋል፡፡

ethiopian breaking news and analysis
ethiopian news
ሰበር ዜና

Loading comments...