የመላእክት ተፈጥሮ

2 months ago
20

ቅዱሳን መላእክት በእለተ እሁድ  በመጀመሪያው ሰዓት ተፈጥረዋል፡፡
እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥር
<<እምኅበ አልቦ ኅበቦ>> ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ፈጥሮአቸዋል፡፡
አፈጣጠራቸውም እንደሰው በነቢብ /በመናገር/ ሳይሆን በአርምሞ /በዝምታ/ ተፈጥረዋል፡፡
ሊፈጥራቸው አስቦ ፈጠራቸውም የተፈጠሩበትም ዓላማ የሰውን ልመና፣ ንስሐ ወደእግዚአብሔር፣የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው ለማድረስና መንፈሳዊ ሥራ ለመስራት እግዚአብሔርን ለማመስገን ተፈጥረዋል፡፡

የቅዱሳን መላእክት የተፈጥሮ ሁኔታ
/ኩነተ ተፈጥሮ/
ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ኢመዋትያን /የማይሞቱ/ ናቸው፡፡
ዝንተ ዓለም በቅድስና ቆመው እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ይኖራሉ፡፡
ቅዱሳን መላእክት ፈጻምያነ ፈቃድ ናቸው የእግዚአብሔርንና የሰውን ፈቃድ ሲፈጽሙ ይኖራሉ፡፡
ቅዱሳን መላእክት (አልቦ ፍፃሜ ለመዋዕሊሆሙ) ለዘመናቸው ፍፃሜ አይነገርላቸውም፡፡
ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ከእሳትና ከነፋስ ነው፡፡
መዝ 103¸4
<<መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዩቹን የእሳት ነበልባል>> እንዲል፦
ነገር ግን ከእሳትና ከነፋስ ተፈጠሩ ሲል ግብራቸውን ለመግለፅ እንጂ እንደምናየው እሳትና ነፋስ ቢሆኑ ኖሮ እንደእኛ ሰዎች ፈርሰው በስብሰው በቀሩ ነበር፡፡
ነገር ግን ከእውነተኛ አምላክ ብርሃን ተፈጥረዋልና
እሳት
ብሩህ ነው።
መላዕክት ብርሐነ አዕምሮ ናቸው
ኃያል ነው
ኃያላን ናቸው።
የመይመረመር ረቂቅ ነው
የማይመረመሩ ረቂቃን ናቸው።
ነፋስ
ፈጣን ነው።
መላዕክት ለተልዕኮ ፈጣኖች ናቸው።
ነፋስ ረቂቅ ነው
መላዕክት ረቂቃን ናቸው።

መሆናቸውን ለመግለጽ ከእሳትና ከነፋስ ተፈጠሩ ይላቸዋል፡፡

Loading comments...