ሠምና ወርቅ ፡ ዱዳዔል

2 months ago
263

በዚህች የዐየር ንብረቷ -89.2°c / -129°F በሆነባት ፍጥረት ሊኖርባት በማይችል በጥንት ስሟ ዱዳዔል ዛሬ አንታርቲካ በምትባል ሲበዛ እጅግ እጅግ ቀዝቃዛ በሆነች ምድረበዳ ውስጥ የአለማችን ትልቁ ምስጢር ይገኛል ።
ካለነሱ ፍቃድና ዕውቅና 500 ማይል ሬዲየስ ውስጥ እንድም መርከብ ሆነ ሰው ወደዚች ቦታ ዝር እንዳይል በአሳ ነባሪ ኢንቫይሮመንት ጥበቃ ስም ህግ አውጥተው በተለያዩ ሀገራት የባህር ሃይል ክልልሉን ያጠሩት ኃያላኑ ሀገራት በጡሩምባዎቻቸው በኩል የሚነፉብንን ግኝታ ግኝቶች ችላ ብለን ከውቅያኖሱ ወደ በረዶአማው ክፍል 800 ማይል ርቀት ወደውስጥ በመግባት ቫስታክ ብለው በሰየሙት ስርፋ ውስጥ በምን ዓይነት የቁፋሮ ፕሮጀክቶች እንደተወጠሩ መልስ ብናጣ ግዜ በቆዳ ብራናዎቻችን ላይ ሺህ አመታትን ያስቆጠሩ ግን ደግሞ ያልተረሱ ጥንታዊ የቤተክርስቲያናት መፅሀፍቶቻችንን ብንጠይቅ ...ዱዳዔል መሆንዋን እንዷ የመፅሀፈ-ሄኖክ ገፅ ውስጥ ተከትባ አገኘናትና ገረመን።

አሁን ማን፥ ምን ወይም እነማንን ለማውጣት ያለ ዕረፍት ሌት ተቀን እየተረባረቡ እንደሆነም ገባን ....' ሆፕ ' ናትኝ

. . . በአዛዝዓል ሥራ ትምህርትም ምድር ሁሉ ጠፋች

ዱዳዔል- ዛሬ ዓለም ለተዘፈቀችበት ግፍ ሰቆቃና መተላለፍ የሆኑ ያልተፈቀዱ ጥበባትና አጠቃቀሞቻቸውን ለሰው ልጆች አሳልፈው መስጠት ምክንያት ናቸው የተባሉና ሌሎችንም ህግጋትን የጣሱ በተማማሉበት በኸርሞን ተራራ ( የፅዮን ተራራ) ግድም የነበሩ ወደ 200* የሚጠጉ ዋና ዋና አመፀኛ ወንጀለኛ ጋንግስተሮች - በቀድሞ ስማቸው ትጉሀን aka ዘ ዋቸርስ- ዋና መሪና አስተባባሪ የነበረው አዛዝዔል በመልዐኩ ሩፋዔል ዕግር ተወርች ተጠርንፎ ከአራት ሺህ ዓመታት በላይ ከሆድዋ ውስጥ በኪሎ ሜትሮች ርቀት ጥልቁ ውስጥ ተቆልፎበት የምትገኝ ቆፋሪዎቹ በኮድ ስሟ ' ሆፕ ' ብለው የሚጠሯት እንደ አልማዝ በጠነከረ በክሪስታል የተዘየደች የበረዶ ዘብጥያ ቦታ እንደሆነችም ጭረን ጭረን ደረስንበት።

መፅሀፈ ሄኖክ ለሌላቸው ሀገሮች በዚህች ቦታ የሚሰራው ለሰው ልጆች የሚጠቅም ሳይንትፊክ ሪሰርች እንደሆነ ነው የሚያውቁት ። እንደ ኢትዮጵያ ላሉ መፅሀፈ ሄኖክ ላላቸው ህዝቦች ደግሞ በምድር ላይ የሚገኙት የእስረኞቹ የውጭ ሴሎች- ማህበራት- የበጎ አድራጎት ድርጅቶች - ኮርፖሬሽኖች -ታላላቅ የዓለማችን ምሁራን እና ሀያላን መንግስቶቻቸው በ 'ሆፕ' ውስጥ ያሉትን አለቆቻቸውን ለማስፈታት (Freez 'em all ) የሚያደርጉት ርብርብ እንደሆነ እንረዳለን ።

* ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋዔልን አዛዝዔልን እጁና እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ አግዘው አለው።
በዱዳዔል ያለች ምድረ በዳዋንም ክፈታት እሱንም በዚያ ጨለማው ውስጥ ጣለው በላዩም እንክብል እንክብል ሸፎ ሻፎ ድንጋዮችን ግጠምበት።
ጨለማንም አልብሰው በዚያ ለዘላለሙ ይኑር ብርሃንን እንዳያይ ፍርድ በሚደረግበት ዕለተ ወደ ገሀነም እንዲሄድ ፊቱን በጨለማ ሸፍነው አለው።
መፅሀፈ - ሄኖክ 3፡ 5-7

* የአማፂዎቹ መሪ አዛዝዔል በዱዳዔል ሲሆን የታሰረው ....ሌሎቹ ደግሞ

ሚካዔልንም እግዚአብሔር ሄደህ ለስሚያዝ ንገረው ....መጨረሻና ፍርዳቸው እስከሚደረግበት ቀን ድረስ የዘላለም ፍርድ እስኪፈፀም ድረስ ሰባውን ትውልድ በምድር ኮረብታ በታች አስረህ አግዛቸው አለው
መፅሀፈ - ሄኖክ፡3፡ 14-15 ... የምገምተው ሁሌም የጠረጥረው ቦታ አለኝ። በዚህ ተራራ ስርፋ ደግሞ ምንም አይነት አትክልት አይበቅልም፤ ጫፉ ላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ባለ አራት ክፍል ትራይ አንግል ያለው ነው፤ ኮምፓሶች በዚህ ቦታ አይሰሩም፤ አውሮፕላኖች በላዩ ማለፍ አይችሉም፤ ለመጎብኘትና ለማሰስ ወደ እርሱ የሄዱ ይጠፋሉ አሌያም ደግሞ እጅግ በፍጥነት ሰውነታቸው ያረጃል(Time) የኢሉሚናተስ ስውራን አለቆች ቤዝ ነው ይባላል... ሌላም ሌላ

Loading 1 comment...