እንፀልይ

1 month ago
57

አባታችን ሆይ 
በአማርኛ
አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትይሁን
የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ
በደላችንን ይቅር በለን
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል
አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን
ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ
መንግሥት ያንተ ናትና
ኃይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ
የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው
ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና
ከተወደደው ልጅሽ ከጌታንችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።

Loading comments...