የዘወትር ፀሎት

2 months ago
71

ዝክረ ቅዱስ ሚካኤል መንፈሳዊ በጎ አድራጎት(መላኩ):
የዘወትር ጸሎት
ውዳሴ ማርያም
 
በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕምርተ 
መስቀል ፊቴንና መላ ሰውነቴን ሶስት
(፫)ጊዜ አማትባለሁ።

፩ እግዚአብሔርን ስለማመን አንድ
አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ
ቅዱስ ስም ልዩ ክቡር ጽሩይ በሆኑ በሦስትነት ወይም በሥላሴ እያመንኩና እየተማፀንኩ ጠላቴ ሰይጣንን እክዳለሁ በዚች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት 
ቁሜ እክድሃለሁ ለዚህም ምስክሬ 
ማርያም ናት በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ

፪አቤቱ እናመሰግንሃለን አቤቱ 
እናከብርሃለን አቤቱ እንገዛልሃለን 
አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመሰግናለን 
ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ አቤቱ እንሰግድልሃለን አንደበትም ሁሉ ላንተ ይገዛል የአምላኮች አምላክ የጌቶ ጌታ የንጉሦችም
 ንጉሥ አንተ ነህ የሥጋም የነፍስም ፈጣሪ አንተ ነህ እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራሃለን።

አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትይሁን
የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ
በደላችንን ይቅር በለን
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል
አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን
ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ
መንግሥት ያንተ ናትና
ኃይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ
የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው
ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና
ከተወደደው ልጅሽ ከጌታንችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።

Loading comments...