ዶር ደብሩ ነጋሽ፡ ሊስልብ የመጣ ጋላ አባባ ቢሉት አይተውም

1 year ago
11

አንድ ማሕበረስብ ስለሌላው ማሕበረስ የሚለው እና የሚናገረው መልካም እና መጥፎ ነገሮች አሉ፡፡ እንዚህም አባባሎች የሚመነጩበት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንዱ በበላይ እና በበታች ማሕበረስብ ያለን ግንኑኘት ለማጠናከር የሚደረጉ አባባሎች ናቸው ፡፡ በተለይ አንዱ የበላይነቱን ይዞ እንዲቀጥል ሌላው የበታችነት እንዲሰማው ለማድረግ፡ በሌላ በኩል አንድ ሕብረተሰብ በእምነትም ሆነ በግባር ከሌላው የተለየ መሆኑን ለማሳየት የሚነግሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ሊሰል የመጣ ጋላ አባባ ብትለው አይተውም የሚለው አባባል በእርግጥም መስለብ የጋላ ባሕል በመሆኑ ለመስለብ ከመጣ ምህረት እንደሌለው ለማሳየት የተባለ ነው፡፡ በሌላ በኩል ፖለቶካኞች ለፖለቲካ ቅስቀሳ ያልተባለው ተባለ ብለው በማሕበረስብ የከፋ ልዩነት ለማምጣት የሚናገሩት ነገር ነው፡ ለምሳሌ ጋላ እና ጋሪ ፒያሳ አይገባም፡ ሲጀመር ፒያሳ የጣሊያን ቃል ነው የተመሰረተውም በጣሊያን ነው ፡፡ እና ከታሪክ አንፃር ይህ አባባል ስንመለከተው ምንም መሰረት የለውም ፡፡ ይህን እና መሰል አባባሎች ምክንያታቸው እና ከበስተጀርባ ስላለው ታሪክ ዶር ዳብሩ ነጋሽ ያብራራልናል ፡፡ አዳምጡት አጋሩት አስተያየት ስጡበት ፡፡

Loading comments...