ኢትዮጵያዊነት ከሀገርና ዜግነት በላይ ነው!

2 years ago
3.3K

ሀገር ከመንግስት በላይ ነው! ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ከዜግነት በላይ ነው! በእርግጥ "ኢትዮጵያ" የሚለው ስርዖ ቃሉ "የላይኛው ዙፋን፣ የላይኛው እውነት" ማለት እንደሆነ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ኤዞፕ በተሰኘው ግጥሙ ላይ ይገልፃል። በዚህ መሰረት ኢትዮጵያዊነት የሚገለጸው ከሀገርና ዜግነት ይልቅ ከመንፈሳዊነት እና እውነት አንፃር ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ለእውነት እና ለህሊና መገዛት ነው። ለሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት፣ የሞራል ልዕልና ያለው ሰው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው።

Loading 29 comments...