ETHIOPIA|Africa : 14 አፍሪካ ሃገራት ❗ለፈረንሳይ❗የቀኝ ግዛት ታክስ | እንደሚከፍሉ ታውቃላችሁ⁉ ወንጀለኞቹ-ሕግጋትንስ?

2 years ago
11

"we prefer freedom in poverty to opulence in slavery"
#Colonial_Tax #Compulsory_Solidarity #France #Africa #NoMore #financial_Liability #500billion$ #the_franc_for_french_a_African_colonies
#Sylvanus_Olympio

ቤኒን ፣ ቡርኪናፋሶ ፣  ጋቦን ፣ ጊኒ-ቢሳው ፣ አይቮሪ-ኮስት ፣ ኮንጎ - ብራዛቪል ፣ ማሊ ፣ ኒጀር ፣ ሴኔጋል ፣ ቶጎ ፣
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ ኢኳቶሪያል-ጊኒ ፣ ካሜሩን እና ቻድ

በ፲፬ አፍሪካ ሃገራት ላይ ፣ ፈረንሣይ የጫነቻቸው ወንጀለኛ-ሕግጋት

እንደምን አላችኹ?! የቱካኤል ቻናል አድማጭ ተመልካቾች ፣
ሠላማችኹ በያላችኹበት ኹሉ ይብዛላችኹ!

14 አፍሪካ ሃገራት ለፈረንሳይ የቀኝ ግዛት ታክስ (የግፍ-ግብር) እንደሚከፍሉ ታውቃላችሁ??

ፈረንሣይ የቀድሞ ቀኝ ተገዥ አፍሪካ ሃገራትን ባርነት እና ቅኝ-መዛት ላስገኘላቸው ጥቅም "የቅኝ ግዛት ግብር" ወይም Colonial Tax የተባለ እጅግ ግፈኛ ክፍያ እንዲከፍሉ ታስገድዳለች።

ዛሬ ስለዚኽ የግፍ ግብር እና እስካኹንም አፍሪካ በአስከፊ ቀኝ-ግዛት ውሥጥ እንዳለች አስረጂ የሆነ ፅሁፍ እናቀርብላችኋለን እስከመጨረሻ በመከታተል ከወደዳችኹት ላይክ በማድረግ እና ሌሎች ሰዎችም መረጃው እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ እንድትተባበሩ ለቻናሉም አዲስ የሆናችኹ Subscribe እንድታደርጉ እየጠየቅን ወደ መረጃው እናምራ ፣

በፈረንሳይ አስገዳጅነት #Colonization_tax የተባለ ወራዳ የታክስ አይነት ድሃ አፍሪካ ሃገራት ከቀኝ ግዛት ከተላቀቁም በኃላ እንኳ ፣ ከሚዘረፉት አንጡራ የተፈጥሮ ሃብት በተጨማሪ ረብጣ ዶላርም ከ1960-አሁን 2020 ድረስ ለፈረንሣይ ታክስ እየከፈሉ ይገኛሉ።

ቤኒን ፣ ቡርኪናፋሶ ፣  ጋቦን ፣ ጊኒ-ቢሳው ፣ አይቮሪ-ኮስት ፣ ኮንጎ - ብራዛቪል ፣ ማሊ ፣ ኒጀር ፣ ሴኔጋል ፣ ቶጎ ፣
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ ኢኳቶሪያል-ጊኒ ፣ ካሜሩን እና ቻድ ናቸው።

   ይህ በጥንቃቄና በዘዴ የተዋቀረ "Compulsory Solidarity" ወይም "አስገዳጅ አብሮነት" በተባለ ጠርናፊ ዘዴ 14 የአፍሪካ ሃገሮችን ያካተተ ሲሆን፣
ግዴታውም :- በቀኝ ግዛትና በባርነት ወቅት ፈረንሳይ ለገነባቻቸው መንገዶች ፣መሰረተ ልማቶች እና ላወጣቻቸው ወጪዎች ካሳ ይሆናት ዘንድ - ከነዚህ አፍሪካ ሃገሮች ከውጭ ምንዛሪና ተቀማጫቸው ላይ 65% ለፈረንሳይ ቀጥታ ወደ ባንኳ Treasury ድጎማ 500billion$ ያስገቡላታል።

ይህ ብቻ ሳይሆን 20% financial Liability (ተጠባባቂ ገንዘብ ) ይከፍላሉ ።
ይህ ማለት ከጠቅላላ ገቢያቸው 15% ብቻ ነው ለራሳቸው ሚያውሉት ማለት ነው።

ለራሳቸው ጉዳይ ገንዘብ ካስፈለጋቸውም ፣ ከፈረንሳይ መንግስት የራሳቸውን ብር መልሰው ይበደራሉ።

ይህ እንግዲህ ከ1960 እ.ኤ.አ ጀምሮ እየተተገበረ ያለ ግፍ ነው።

#ለምን_አንከፍልም_አይሉም?

ቀላል የሚመስል ጥያቄ ነው። ሴራው ግን ውስብስብና በተንኮል የታጨቀ ግፍ ነው።

እ.ኤ.አ. በ 1958 የጊኒው ፕሬዝደንት ሴኩ ቱሬ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ለመውጣት ወስኖ እና የሀገሪቱን ነፃነት መረጠ ።

"አልከፍልም እንቢ!" አለ። ከኮሎኒ-ኢማፓየርም እራሱን አገለለ።

በፓሪስ ያሉት የፈረንሳይ ቅኝ ገዥ ልሂቃን በጣም ተናደዱ! እጅግም ተቆጡ ፣  ፈረንሣይ በቁጣ ብቻ አላለፈችውም
በጊኒ የሚገኘው የፈረንሳይ አስተዳደር ፣ በጊኒ የሚገኘውን "የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ጥቅማጥቅሞች የሚወክሉ" የሚሏቸውን ሁሉንም ነገር አጠፉ።

በጊኒ ያለው የፈረንሳይ ጦርና አስተዳደር ሁሉንም ነገር "በፈረንሳይ ኃብት የተገነባ" ያሉትን ሁሉ ማውደም ጀመሩ።

ሦስት ሺህ ፈረንሣውያን ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሁሉ አንድም ሳይቀራቸድ ጠራርገው ወስደው ማንቀሳቀስ የማይችሉትን እያወደሙ ከሀገሪቱ ወጡ።

ማንቀሳቀስ የማይችሏቸውን ትምህርት ቤቶች፣ የችግኝ ማረፊያ ጣቢያዎችን ፣ የሕዝብ አስተዳደር ሕንፃዎች እና መንገዶችን አፈራረሱ ፣ አወደሙ።

መኪኖች፣ መጻሕፍት፣ ሕክምና፣ የምርምር ተቋም መሣሪያዎች፣ መድኃኒቶችን ፣ ትራክተሮች ሰባበሩ፣ አበላሹ አቃጠሉ።

ፈረሶች፣ በእርሻ ቦታዎች ውስጥ ያሉ እንስሳትና እና ላሞች ተገድለዋል፣ በመጋዘን ውስጥ ያሉ ምግቦች ፣ እህሎች ተቃጠሉ ፣ ተመረዙ ፣ የቻሉትንም ዳግመኛ አገልግሎት እንዳይሰጡ መሬት ቆፍረው ቀበሯቻው።

አልከፍልም ብላ ያመፀችውን ጊኒ - እንዳልነበረች አደረጓት።

የዚህ አሰቃቂ ድርጊት ዓላማ ፈረንሳይን አለመቀበል ወይም
"ማንም ሃገር ፈረንሳይ ላይ አምፃለሁ ቢል የጊኒ እጣ እንደሚደርሰው" ማስጠንቀቂያ የፈረንሣይን ትህዛዝ አለመቀበል የሚያስከትለው መዘዝ በጣም ከፍተኛ እንደሚሆን ለሌሎች ቅኝ ግዛቶች ሁሉ ግልጽ መልእክት ለማስተላለፍ ነበር።

በዚኽም ቀስ በቀስ ፍርሃት በአፍሪካ ልሂቃን እና ሃገራት ዘንድ ተስፋፋ፣
እናም ከጊኒ ክስተት በኋላ የትኛውም ሃገር "እምቢ!" የማለት ድፍረት አላገኘም ፣ የሴኩ ቱሬ ምሳሌን ለመከተል፣ አቅማሙ።

የጊኒው ሴኮ ቱሬ "we prefer freedom in poverty to opulence in slavery"  ወይም "በባርነት ከመኖር በድህነት ውስጥ ነፃነትን እንመርጣለን"  የሚለውን እምቢ-ባይ መፈክር በፈረንሣይ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ካሉት አፍሪካ ሃገራት ውስጥ አንዱም በፍርሃት ሊያስቀጥለው አልወደደም።

በ 612$ የተጠናቀቀው "ርካሹ" መፈንቅለ-መንግስት ጉዳይ

በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ትንሽ ሀገር የቶጎ ሪፐብሊክ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሲልቫኑስ ኦሊምፒዮ ከፈረንሳይ ጫና ሊያላቅቀው የሚችል መላ ዘየደ ፣ መፍትሄ አገኘ ፣ አበጀ።

ሀገሩ የፈረንሳይ የመጫወቻ ሆና እንድትቀጥል አልፈለገም ስለዚህ የቅኝ ግዛትን ቀጣይነት ስምምነት "ደ ጎል" (De Gaule) ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆነም ፣ ነገር ግን ቶጎ ከፈረንሳይ ቅኝ-ግዛት ለምታገኘው ጥቅም ፣ ለፈረንሳይ አመታዊ ዕዳ ለመክፈል ተስማማ።

ይኽም ፈረንሳዮች ከመሄዳቸው በፊት ሀገሪቱን ልክ ጊኒ ላይ እንዳደረጉት ቶጎንም እንዳያጠፏት መደራደሪያ ብቸኛው ቅድመ ሁኔታ ነበር።

ይሁን እንጂ በፈረንሳይ የተገመተው "የቅኝ ግዛት ዕዳ" ተብሎ የሚጠራው ገንዘብ ማካካሻ መጠን በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ እኤአ 1963 ከነበረው ከቶጎ በጀት 40% ያኽል ይጠጋል።

በዛ ላይ አዲስ ነፃ የሆነችው ቶጎ የፋይናንስ ሁኔታ በጣም ያልተረጋጋ ነበር ፣

ስለዚህ ከዚኽ አጣብቂኝ ሁኔታ ለመውጣት የቶጎ ፕሬዝደንት ኦሊምፒዮ የፈረንሳይ የቅኝ ግዛት ገንዘብ FCFA (the franc for french a African colonies) ከተባለው ለፈረንሳይ የአፍሪካ ቅኝ ግዛቶች ከሚያገለግል መገበያያ ፍራንክ ለማውጣት እና ሃገሩ ቶጎ የራሷ መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራት ወሰነ።

እ.ኤ.አ. ጥር 13 ቀን 1963 የአገሩን ገንዘብ ማተም ከጀመረ ከሶስት ቀናት በኋላ በፈረንሳይ ድጎማና ግፉ ባይነት የተደገፉ፣  ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ወታደሮች ቡድን ፣ አዲስ ነፃ የወጣችውን ቶጎ የመጀመሪያ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ፈረንሣይ ባሰማራቻቸው ፣ በደለለቻቸው በሃገሩ ልጆች ተገደለ ።

green)

French North Africa

French Morocco(now Morocco)

French Algeria 

French Tunisia  (Tunisia)

French West AfricaEdit

Ivory Coast 

Dahomey or French Dahomey (now Benin)

Independent of Dahomey,

Porto-Novo 

Cotonou 

French Sudan (now Mali)

Senegambia and Niger 

Guinea or French Guinea 

Mauritania Niger 
Sultanate of Damagaram (Zinder)

Senegal 

French Upper Volta (now Burkina Faso)

French Togoland  (now Togo)

Gambia

French Equatorial AfricaEdit

Chad 

Oubangui-Chari (currently Central African Republic)

Present-day The Republic of Congo, then French Congo 

Gabon 

French Cameroon  current Cameroon

São Tomé and Príncipe 

East Africa and Indian Ocean

Madagascar 

Kingdom of Imerina 

Isle de France (1715–1810) (now Mauritius)

Djibouti (French Somaliland) (the French Territory of the Afars and the Issas) (French Somalia) (1862–1977)

Mayotte (1841–present)

Seychelles (1756–1810)

Chagos Archipelago (1721–1745, 1768–1814)

Comoros 

Réunion

Loading comments...